በየቤቱ የሚደረግ ሽያጭ

Skip listen and sharing tools

If this page does not display correctly, download a copy instead: Door-to-door sales - Amharic (PDF, 169KB).

በአውስትራሊያ ውስጥ ያለዎት መብቶች

በየቤቱ የሚደረግ ሽያጭ ምን ማለት ነው?

በዚህህ ሊያካትት የሚችለው ሰዎች:

 • የቤት እቃዎችን ሊሸጡልዎ ሲሞክሩ
 • በርስዎ ቤት ጥገናዎችን ለማካሄድ ሲጠይቁ
 • የጋዝ፣ ኤሌትሪክሲቲ፣ ተለፎን ወይም የኢንተርኔት አቅራቢዎችን እንዲቀይሩ ሲጠይቁ ይሆናል።.

ሽያጭ የሚያካሂደው ሰው በቤቴ በራፍ መቸ ነው መምጣት የሚችለው?

ይህ ሽያጭ ሰውየ ወደ ቤትዎ በራፍ መምጣት የሚችለው:

 • ጥዋት ሰዓት 9am እና ከሰዓት በኋላ 6pm ከሰኞ እስከ ዓርብ ባለው ጊዜ
 •  ቅዳሜ ጥዋት ሰዓት 9am እና ከሰዓት በኋላ 5pm ይሆናል።

እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ጊዜ መምጣት አይችሉም።.

ይሁን እንጂ አቅራቢ ድርጅቱ ከርስዎ ጋር ከተስማማ በማንኛውም ጊዜ መጎብኘት ይችላል።

ሽያጭ የሚያካሂደው ሰው ምን ዓይነት ደንቦችን መከተል አለበት?

ወደ ቤትዎ በር በሚመጡበት ጊዜ የሽያጭ አቅራቢው ሰውየ:

 • ለምን እንደመጡ ለርስዎ መናገር አለባቸው
 • ስማቸውንና የሚሠሩበትን ኩባንያ ለርስዎ መናገር አለባቸው
 • እንዲሄዱ ከነገሯቸው መሄድ እንዳለበት መናገር (ለሺያጩ ሰውየ እንዲሄድ ከጠየቁት ቢያንስ ለ30 ቀናት የሚሆን ማነጋገር የለበትም)
 • የተደረገውን ስምምነት የመሰረዝ መብት እንዳላቸው መናገር (ይህም እንዴት ስምምነቱን መሰረዝ እንደሚችሉ)
 • ማንኛውም ስምምነት በሚካሄድበት ጊዜ የሺያጩ ሙሉ አድራሻ ዝርዝርና ፊርማ የሽያጭ አቅራቢዎችን በመወከል ማካሄድ አለበት
 • በማንማውም ስምምነት ላይ ከመፈረሙ በፊት የጽሁፍ ቅጅ ወረቀት ለርስዎ መስጠት አለበት
 • ስምምነቱ በተፈረመ በ10 ቀናት ውስጥ ክፍያን አለመጠየቅ
 • ስምምነቱ በተፈረመ በ10 ቀናት ውስጥ ከ$500 ዶላር በላይ ለሚያወጣ እቃ መስጠት የለባቸውም
 • ስምምነቱ በተፈረመ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አገልግሎቶችን አለማቅረብ ይሆናል።.

የሽያጭ ሰውየው ስለሚያቀርበው ማንኛውም ነገር ደስተኛ አይደለሁም … ምን ማድረግ እችላለሁ?

 • ‘አመሰግናለሁ አልፈልግም’ ማለት .
 • በቤትዎ በር ላይ ከሆነ ሰው ማንኛውንም እቃ ለመግዛት መጨናነቅ የለብዎም።

አንድ የሚሽጥ ሰው መጥቶ- በጣም ጥሩና ትክክለኛ እቃ ነው ብሎ ቢደራደር ሁልጊዜ ‘አይሆንም’ ማለት ነው

 • የሽያጭ ድርድሩን ፍጹም ትክክለኛ አስመስሎ ማቅረብ
 • የሆነ እቃ ወይም አገልግሎት ሳያቀርቡ ክፍያ ሲጠይቁ
 • እርስዎ እንዲበሳጩና እንዲናደዱ የሚያደርግ ባህሪ ሲያሳዩ እምቢ ማለት ነው።

ሰዎች ከመንግሥት አካል እንደመጡ አድርገው ያስመስላሉ

 • በቤትዎ በር የሆነ ሰው መጥቶ ከመንግሥታዊ ድርጅቶች- ማለት እንደ ከአውስትራሊያ ግብር ጽህፈት ቤት ወይም ከሴንተርሊንክ ነው የመጣን ብለው ሲናግሩ።
 • የርስዎን የባንክ ዝርዝር ሁኔታ ወይም የርስዎን ግላው መረጃ መጠየቅ፣ ለምሳሌ፡ የርስዎን የታክስ/ግብር ተመላሽ ለመክፈል ወይም የሴንተርሊንክ አበል መጨመር።
 • እነዚህን ዝርዝር መረጃዎች በመጠቀም የርስዎን ገንዘብ ወይም የርስዎን መታወቂያ መስረቅ ይችላሉ።.
  ማሳሰቢያ: የሆነ ሰው በቤትዎ በር ላይ መጥቶ እና ከመንግሥት ድርጅት ነው የመጣሁት ካለ ጥንቃቄ ማድረግ ነው። ሁልጊዜ የነርሱን መታወቂያ መጠየቅ። በአብዛኛው ጉዳዮች ላይ የመንግሥት መምሪያ ድርጅቶች በዚህ ዓይነት መንገድ አያነጋግሩም።

የሽያጭ ሰውየው በሚያቀርበው ነገር ደስተኛ ነኝ … ምን ማድረግ አለብኝ?

ከሽያጩ ሰውየ የሆነ ነገር ለመግዛት እሺ ካሉ የስምምነት ወረቀት ላይ እንዲፈርሙ ይጠየቃሉ። ስምምነቱ መሆን ያለበት:

 • በግልጽና በቀላል ቋንቋ የተጻፈ መሆን አለበት
 • ቅድመሁኔታዎችን በሞላ ያካተተ መሆን አለበት
 • ጠቅላላ ዋጋውን ወይም እንዴት እንደተሰላ ያካተተ መሆን አለበት
 • የፖስታ ወይም የመላኪያ ክፍያዎችን ያካተተ መሆን አለበት
 • የሽያጩን ስምና አድራሻ ዝርዝር የያዘ መሆን አለበት
 • የአቅራቢውን ዝርዝር ማለት አድራሻና የስልክ ቁጥር ያካተተ መሆን አለበት።
 • በርስዎና በሽያጩ መፈረም አለበት
 • በግልጽ የተጻፈ ወይም የታተመ መሆን አለበት (ሆኖም የሆነ ለውጥ ካለ በእስክብሪቶ በመጻፍ መፈረም አለበት)
 • ስምምነቱን ለመሰረስ ስለሚኖርዎት መብቶች መረጃ ያካትታል
 • በቀላሉ ለመረዳት
 • ሀሳብዎን ከቀየሩ ስለሚኖርዎት መብቶች የሚገልጸውን ቅጽ ይዞ መምጣት።

ማሳሰቢያ: እንግሊዝኛ በደንብ የማይናገሩ ከሆነ ታዲያ ሽያጩ ሰውየ ልጅዎን እንደ አስተርጓሚ አድርጎ በመጠቀም የስምምነት ወረቀት ማስፈረሙ ትክክለኛ አይደለም። በማንኛውም የስምምነት ወረቀት ላይ ከመፈረምዎ በፊት በራስዎ ቋንቋ የተጻፈ ስምምነት ቅጂ ወረቀት እንዲሰጥዎ መጠየቅ አለብዎት።

ስምምነቱ ፈርሜያለሁ ነገር ግን ሃሳቤን ቀይሬያለሁ … ምን ማድረግ እችላለሁ?

በየቤቱ እየሄደ ከሚሸጥ ሰውየ ከ$100 ዶላር በላይ የሚያወጣ እቃ ወይም አገልግሎት ለመግዛት ከተስማሙ ስለ ስምምነቱ ሃሳብዎን ለመቀየር የ10 የሥራ ቀናት ይኖርዎታል። ይህም ‘የሃሳብ መቀየሪያ ጊዜ’ ተብሎ ይጠራል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያደረጉት ውሳኔ ትክክለኛ አይደለም ካሉ ያለምንም ክፍያ የግዢውን ውል ማፍረስ ይችላሉ። .

እርስዎ ከመስማማትዎ በፊት ሽያጩ ሰውየ ይህ መብት እንዳለዎት ማሳወቅ አለበት። በዚህ የሃሳብ መቀየሪያ ጊዜ ውስጥ የመግዛት ውሉን መቀየር ከፈለጉ ታዲያ ሽያጩ ሰውየ ወይም አቅራቢ ድርጅቱ ስለሚከተሉት ማድረግ አይፈቀድላቸውም:

 • የርስዎን የሃሳብ መቀየሪያ ጊዜ እንዲሰርዙ መጠየቅ
 • በስምምነቱ ላይ እሺ እንዲሉ ጫና መፍጠር
 • ለመሰረዝ የክፍያ ዋጋ መጠየቅ።.

ስምምነቱን በቃል ወይም በጽሁፍ አድርጎ መሰረዝ ይቻል ይሆናል።.

በቤትዎ በር ላይ የሆነ ሰው መጥቶ የጋዝ ወይም የኤሌትሪክሲቲ አቅራቢዎችን ለመቀየር ከፈለጉ ሲጠይቅዎ

 • የእነሱ ኩባንያ ታላቅ የገንዘብ ቅናሽ እንዳላቸውና ገንዘብ እንደሚያተርፉ ይነግሩዎታል። .
 • በስምምነት ወረቀቱ ላይ ወዲያውኑ እንዲፈርሙ የሽያጭ ሰውየ ያጣድፍዎታል።
 • ስለሚጨነቁ ይፈርማሉ።
 • በሚቀጥለው ቀን የተደረገውን ድርድር እንደማይፈልጉት ይወስናሉ።.

ማሳሰቢያ:

 • በስምምነቱ ላይ ለመፈረም አይጨነቁ፤ መረጃዎችን እንዲያነቡ ሽያጩ ሰውየ ትቶልዎ እንዲሄድ መጠየቅ ይችላሉ።
 • ከፈረሙና ከዚያም ሃሳብዎን ከቀየሩ፤ የሃሳብ መቀየሪያ ጊዜ ገደብ መብት አለዎት።
 • ሃሳብዎን እንደቀየሩ ለሽያጭ ኩባንያው ለመናገር በ10 ሥራ ቀናት ውስጥ ማነጋገር።
 • ሃሳብዎን ስለቀየሩ የሽያጭ ኩባንያው ምንም ክፍያ ማካሄድ አይችልም።

በየቤቱ እየሄዱ ስለ ሽያጭ አግባብ አለመሆን በበለጠ ዝርዝር ለማግኘት በድረገጽ www.scamwatch.gov.au ላይ መሄድ።