የገዚዎች መብት

Skip listen and sharing tools

If this page does not display correctly, download a copy instead: Your shopping rights - Amharic (PDF, 211KB).

የእርስዎ መብት በአውስትራሊያ የሸማቾች መብት ህግ የፋከትሺት

መቼ ነው ተመላሽ ማግኘት የምችለው?

በገዙት እቃ ላይ ችግር ካለው፣የገዙበት ሱቅ የእቃውን ምትክ፣ የገንዘብ መመለስ፣ የጥገና አገልግሎት ወይም ሌላ አይነት መላ መፍጠር አለበት፡፡ እንደ ችግሩ ሁኔታ የመፍትሄ አይነቶች ይቀርባሉ።

ሱቁ ምን አይነት ችግሮችን መፍታት ይችላል?

የተበላሸ

እቃዎችና አገልግሎቶች ተቀባይነት ያለው ጥራት እንደሚኖራቸው መጠን የተበላሸን እቃ ለመመለስ ይፈቀድልዎታል።

አንድ እቃ የተበላሸ የሚባለው:

 • እቃው መስራት ያለበትን ነገር በደንቡ ካልሰራ – ለምስሌ, ዳቦ መጥበሻው ካልጠበሰ
 • ችግር ካለበት – የዳቦው መጥበሻ ማዞሪያ ወዲያው እንደተገዛ ወለቀ
 • የእቃው አጨራረስ ተቀባይነት የለውም – የዳቦው መጥበሻ ጭረት አለው፡፡
 • ደህና አይደለም – ከዳቦ መጥበሻው ላይ እሳት ይፈናተራል፡፡
 • እድሜ የለውም – የገዛሁት የዳቦ መጥበሻ ከገዛሁት በኋላ በሶስት ወሩ ተሰበረ.

ይህ ከሆነ እቃዎን (እቃዎ) የመመለስ መብት አይኖርዎም:

 • ከመግዛትዎ በፊት እቃው ችግር እንዳለው ሱቁ ከነገረዎ (ምልክት ካለበት)
 • እርስዎ እቃውን ከመግዛትዎ በፊት እቃውን አገላብጠው አይተው ማዬት የሚገባዎትን ችግር ካላዩ
 • አቃዎን መጠቀም ካለበት ውጭ ከተጠቀሙ ወይም
 • እቃውን ለረጅም ጊዜ ከተጠቀሙበት፡፡

ችግር መኖሩን ያወቅሁት እቃውን ከተጠቀምኩበት በኋላ ነው፡፡

ምንም እንኳን የሚከተለው ቢሆንም የተበላሸውን እቃ መመለስ ይችላሉ:

 • ካረጀ ወይም ከተጠቀሙበት
 • ዋጋው ወይም ምልክቱ ቢገነጠልም ወይም
 • መጀመሪያ የመጣበት ማሸጊያ ካርቶን ባይኖርም፡፡

ሸሚዝ ገዝቼ ትንሽ ቀናት ለበስሁት ሳጥበው ግን ምንም እንኳ የተለጠፈውን መመሪያ ብከተል ቀለሙ እዬለቀቀ አስቸገረኝ፡፡

ለናሙና ከተቀመጠው ሞዴል ጋር አይመሳሰልም::

ባለው ናሙና መሰረት እቃ ከገዙ ዋናው እቃ ከናሙናው ጋር መመሳሰል አለበት፡፡ የገዙት እቃ ግን የተለዬ ከሆነ እርስዎ የማስመለስ መብትዎ የተጠበቀ ነው፡፡

በጠቀመተጠው ናሙና ጨርቅ መሰረት ሶፋ አዘዝሁ ሶፋው ሲመጣ ግን ቀለሙ እኔ ካዬሁት ናሙና ውጭ ነው፡፡.

ስለቃው ከተነገረለት ጋር አይዛመድም፡፡

እቃው ሰለተነገረት ወይም መግለጫ ከተደረገለት ጋር አይዛመድም (ለምሳሌ, ከምልክት አሰጣጥ ላይ ወይም በቲቪ ከታዬው ማስታዎቂያ ጋር). የተገዛው እቃ ከተነገረለት ወይም ከተባለለት የተለዬ ከሆነ እርስዎ ገንዘብዎን ማስመለስ መብትዎ ነው፡፡

ከሱቁ ማውጫ ላይ ያለውን ዝርዝር አይቼ ከቆዳ የተሰራ ቦርሳ ገዛሁ፣ ቤት ሄጄ ሳዬው ግን ከቫይናል ጎማ የተሰራ ነው፡፡.

አሻሻጩ የተናገረው ተግባራዊ አይደለም።

እቃው አሻሻጩ ያደርጋል ብሎ የነገረዎን ተግባር የማያከናውን ከሆነ ገንዘብዎን የማስመለስ መብትዎ የተጠበቀ ነው፡፡

ሰዓት ገዛሁ፣ አሻሻጩ እንደነገረኝ ሰዓቱን አድርጌ ውሃ ውስጥ መስመጥ ትችላለህ ነው፣ ነገር ግን ሰዓቱን አስሬ ባህር ውስጥ ስገባ ሰዓቱን ውሃ ሞላበት፡፡.

እኔ ለጠየኩት አይሰራም። (የጠየቅሁትን አይሰራም፡፡)

ስለሚከተለው ለየት ያለ ስራና ዓላማ ካልሰራ እቃውን መመለስ ይችላሉ።ይህም፡

 • ከመግዛትዎ በፊት ለአሻሻጩ እቃውን ለምን እንደፈለጉት ከተናገሩ እና
 • እቃውን ሲመርጡ በሱቁ ምክር ላይ ተመርኩዘው ከሆነ::

ለመኪና ሻጩ እኔ የምፈልገው መኪና ጀልባ የሚጎትት ነው ብዬ ነው፡፡ያልሁትን ይሰራል በማለት እርሱም አንድ ሸጠልኝ :: ማታ የመኪናውን መረጃ ሳነብ መኪናው ጀልባ እንደማይጎትት ተረዳሁ፡፡

ሃሳቤን ቀይሬአለሁ

እርስዎ ሃሳብዎን ሰለቄሩ ብቻ ሱቁ እቃውን አይመልስም። ነገር ግን፣ አንዳንድ ሱቆች የራሳቸው የሆነ የውስጥ መመሪያ ሊኖራቸው ሲችል ይህም እቃን ለመመለስ ወይም ለወደፊቱ ሌላ እቃ እንዱገዙ ነጥብ መያዝ ይሆናል።

ደረሰኙ የለኝም፡፡

እቃውን ከዚያ ሱቅ የመግዛትዎ ማረጋገጫ ያስፈልግዎታል፡፡. እቃ የገዙበት ገንዘብ ደረሰኝ ከሌልዎ እነዚህን ማሳዬት ይችላሉ፣ ለምሳሌ:

 • የክሬዲት ካርድ ስቴትመነት
 • የቀብድ/የሌይ ባይ ስምምነት
 • የመግዛትዎ ማራጋገጫ ቁጥር በኢንተርኔት ወይም በስልክ የገዙ ከሆነ።

እቃውን ያገኘሁት እንደ ስጦታ ነው፡፡

የስጦታ ደረሰኞች ልክ እንደገዢ ደንበኛ ለማስመለስ መብት አላቸው – መመለስ የሚችሉት የገዙበት ማረጋገጫ ካለዎት ነው፡፡ ከላይ ይመልከቱ፡፡

የገዛሁት ሽያጭ ላይ እያለ ነው፡፡

እርስዎ ልክ በሙሉ ዋጋ እንደተገዛው እቃ የመመለስ መብት አለዎት። ለዚህ ነው መመለስ የማይቻልን እቃ በሽያጭ የሚል ጽሁፍ መለጠፍ ህገ ወጥ የሆነው፡፡

ነገር ግን ሱቁ ችግር መኖሩን ነግረዎት አውቀው ለሚገዙት እቃ ወይም እርስዎ ሲመረምሩ ችግር መኖሩን አውቀው ለገዙት መመለስ አይችሉም፡፡ ለምሳሌ ከናቲራው ላይ ያለው ታግ ቅናሽ ያገኙት ብልሽት ስላለው ነው ብሎ ካመለከተ ነው፡፡

ለምሳሌ ሽያጭ ላይ ያለ እቃዎች የሚያካትተው

 • ቅናሽ ላይ የወጣ
 • በናሙና እና በአሮጌ እቃ ማንጠልጠያ ላይ ያለ
 • ከፋብሪካ መሸጫ የተገዛ ይሆናል።

አሮጌ የሰራ እቃ ነው የገዛሁት

ከሱቅ ከሆነ: ልክ አዲስ እቃ ሲገዙ ያለዎት መብት አሮጌም እቃ ሲገዙ መብቱ አለዎት, ነገር ግን እቃውን ሲገዙ የእቃውን ሁኔታ፣እድሜ እና ዋጋ ከግንዛቤ ማስገባር አለብዎት.

ከግለሰብ ሻጮች: ሻጩ የገዙትን እቃ የመመለስ፣ የመተካት ወይም የመጠገን ግዴታ የለበትም(ለምሳሌ ከጋራጅ ሴል ወይም በምደባ (ከእንሸፃለን) ማስታዎቂያ በኩል የገዙት ከሆነ)፡፡

ከኢንተርኔት ላይ ገዛሁት፡፡

እቃውን የገዙት አውስትራልያ ውስጥ ካለ የኢንተርኔ ድርጅት ከሆነ ልክ ከሱቅ እንደገዙት ያለወት መብት የተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን የገዙት ከግለሰብ ካልሆነ በስተቀር፡፡ ከላይ ይመልከቱ፡፡

ለተሰጠው መላ ከተስማማሁ፣ እቃውን የመመለስ፣ የጥገና አገልግሎት ወይም ገንዘቡን የማስመለስ መብቴ የተጠበቀ ነው?

እንደ ችግሩ አይነት ይለያያል፡ ይህም

ከፍተኛ – ሊጠገን የማይቻል ወይም ለመጠገን አስቸጋሪ የሆነ ከነዚህ

መምረጥ ይችላሉ:

 • እቃውን መመለስ እና ገንዘብዎን መቀበል ወይም ምትኩን መቀበል ወይም
 • እቃውን ለራስዎ አድርገው የእቃው ዋጋ የወረደበትን መጠን መተዬቅ

ቀላል– አግባብ ባለው ጊዜ ሊጠገን ይችላል

ለሱቁ እቃውን እንዲጠግነው እድል መስጠት ይእላሉ፡፡ አነሱ እቃውን መተካት፣ መጠገን ወይም ገንዘብዎን መመለስ ይችላሉ፡፡. ሱቂ እቃውን መጠገን እንፈልጋለን ካለ፣ እቃውን ለፋብሪካው እንዲጠገን የመመለስ ሃላፊነት የራሳቸው ነው (ከመመሪያ ጋር)፡፡

ሱቁ እቃውን ለመጠገን ወይም ለመመለስ ከሚገባው በላይ ከወሰደ፡

 • እቃውን ወስደው ገንዘቡ እንዲመለስ ወይም ሌላ እንዲተካልዎት መጠዬቅ, ወይም
 • ሌላ እቃውን የሚጠግን ሰው ፈልጎ እቃው የተሰራበትን ተመጣጣኝ ክፍያ ሱቁ እንዲከፍል ማድረግ፡፡