የሞባይል ስልክ ኮንትራት ውል - ለደንበኞች ምክሮች

Skip listen and sharing tools

If this page does not display correctly, download a copy instead: Mobile phone contracts - Amharic (PDF, 389KB).

ሞባይል ስልክ ከመግዛትዎ በፊት

እነዚህን ስያሜዎች መረዳት:

  • አገልግሎት አቅራቢ: የርስዎን ሞባይል ስልክ ከነትዎርክ አውታር የሚያገናኝ ኩባንያ ሲሆን ታዲያ ስልክ መደወልና ኢሜል መላክ ይችላሉ።
  • ፕረሚም/premium SMS: ለአገልግሎቶች ማለት እንደ በትክክለኛ ተለቪዥን ላይ ድምጽ መስጠት፣ መወዳደር እና በተወሰነ ጊዜ መክፈልን ስለመግለጽ የሚጠቅም ጽሁፋዊ መልእክት ነው። በፕረሚም/premium SMS መልእክትን ለመላክ ወይም ለመላክ ከመረጡ ለአገልግሎቱ መፈረም እንዳለብዎትና ለስልክ ጥሪ በጣም ውድ በሆነ ዋጋ ሊከፍሉ ይችላሉ። ለመሰረዝም ከባድ ሊሆን እንደሚችልና ከፍተኛ ወጪ እንደሚያስከትል ነዋ።
  • በዓለም አቀፍ ስለሚንቀሳቀስ/international roaming: በውጭ ሃገር ሆነው ሞባይልዎን በመጠቀም የስልክ ጥሪ ለማካሄድ ወይም ለመቀበል። ይህ ዋጋው ሊወደድ ይችላል። የቅድመ ሁኔታዎችን ስለማንበብ ማረጋገጥና ከዚያም ለዚህ አገልግሎት ምን ያህል እንደሚያስከፍል ያውቃሉ።
  • 32GB/16GB: እነዚህ ቁጥሮች ብዙጊዜ በፕላን እቅዱ ውስጥ የተገለጸ ሲሆን ታዲያ የሞባይ ስልክዎን የጥሬ መረጃ መያዝ አቅም ያሳያል እንጂ የቀረውን ጥሬ መረጃ የመክፈት አቅሙን አይደለም።

ውሳኔ:

  • ምን ያህል የስልክ ጥሪ እና በጽሁፍ መልእክት ማካሄድ ይፈልጋሉ
  • ምን ያህል ጥሬ መረጃ ለመያዝ ይፈልጋሉ፡ ለምሳሌ፡ ኢሜል ለማየት ወይም ብዙጊዜ ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ከሆነ በወር ውስጥ ከፍተኛ ጥሬ መረጃ ሊከፍቱበት የሚያስችል ፕላን እቅድ ሊያስፈልግዎት ሲችል - በአብዛኛው በወር 1GB ወይም 2GB ያስፈልጋል። ስለ ጥሬ መረጃ አጠቃቀም የበለጠ መረጃ ለማግኘት በአገልግሎት አቅራቢ ድረገጽ ላይ ማየት።
  • በኮንትራት ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ መቆየት ስለሚፈልጉ። ኮንትራት ውሉ ከ 12 እስከ 36 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ሊሆን ይችላል። ኮንትራት ውሉን ለመፈረም ካላመችዎት፤ በቅድሚያ የሚከፈልበትን አገልግሎት ቀድሞ መሞከር። እንደገና የሚሞላው ካርድ ካለቀ በኋላ ታዲያ በኔትዎርክ አገልግሎት ስለመቆየት ወይም ሌላ ስለመምረጥ ይወስናሉ።

ከዚህ በታች ያለን ያረጋግጡ:

  • ተዘዋውሮ በማየት የተለያዩ ኔትዎርክ አቅራቢዎች ያላቸውን ዋጋዎች፤ ሁኔታዎች እና ፕላን እቅድ ማወዳደር
  • ስለ አገልግሎትና ክፍያዎች ጽሁፋዊ መረጃን ማግኘት
  • ኮንትራት ውሉን ከጣሱ ወይም ከቀየሩ ወይም ስልኩ ከተሰበረ፣ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ ስለሚያስከትለው ወጪ ክፍያ መረዳት
  • በዋስትና ምን እንደተካተተና እንዳልተካተተ የዋስትና መግለጫ ወረቀትን ማንበብ
  • በውጭ ሃገር ሆነው ስልክ ሲጠቀሙ እንዴት እንደሚከፍሉ ማወቅ

ማየት ያለብዎ:

  • በቀላሉ መጠቀም የሚችሉትን ሞባይል ስልክ
  • አቅምዎ ለሚፈቅድልዎ ፕላን
  • በአካባቢዎ ጥሩ የኔትዎርክ ይዘት ላለው አገልግሎት አቅራቢ።

ያስተውሱ:

  • ከኮንትራት ጊዜ ከማለቁ በፊት ለሚሰረዝ አገልግሎት ብዙ ክፍያዎችን ያካሂዳሉ
  • አንዳንድ አገልግሎቶች ተጨማሪ ክፍያዎች ሲኖራቸው ይህም - ለድምጽ መልእክት፣ ጥሪን ለማስተላለፍ፣ ለፕረሚም/premium SMS ጽሁፋዊ መልእክት፣ በኢንተርኔት መረጃ ለመፈለግ እና በዓለም አቀፍ ለተንቀሳቃሽ ስልክ
  • የርስዎን ሞባይ ስልክ በአካባቢው ለመጠቀም የትካተተ ስለመሆኑ በአገልግሎት አቅራቢ ድረገጽ ላይ ማጣራት ወይም በአካል ወደ መጋዘናቸው መሄድ
  • ከተፈቀደው ጥሬ መረጃ በላይ ወይም ከተፈቀደልዎ ስልክ ጥሪ በላይ መጠቀም ተጨማሪ ወጪ ሊያመጣ ይችላል።

በሞባይ ስልክ ላይ ዋስትና

  • ለመግዛትዎ ማረጋገጫ እንዲሆን ደረሰኙንና የኮንትራት ውሉን ማስቀመጥ።
  • ቸርቻሪዎችና አገልግሎት አቅራቢዎች የብድር አቅርቦት የላቸውም ወይንም በዋስትና ጊዜ ስልኩን ለማስጠገን ወይም ለመተካት አይችሉም። ቢሆንም አንዳንዶች ይህንን ለማድረግ ፖሊሲ ደንብ ይኖራቸዋል።
  • ስልክዎ በሚጠገንበት ጊዜ ወርሃዊ ክፍያዎን ለመቀጠል ባለዎት የኮንትራት ውል ቅድመ ሁኔታ ይወሰናል። ስለ ዋስትና የበለጠ መረጃ ለማግኘት የእኛን ዋስትና/Warranties section የሚለውን ክፍል ማየት።
  • እንዲሁም በአውስትራሊያ ተጠቃሚዎች ህግ መሰረት መብቶች አለዎት። የሞባይል ስልክዎ መሥራት ካቆመ፤ ክፍያው እንዲመለስ ወይም እንዲቀየርልዎ መጠየቅ ይችሉ ይሆናል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት የእኛን ክፍያ መመለስ፣ ጥገና እና መቀየር የሚለውን ገጽ ማየት።

ለሞባይል ስልክ ኮንትራት ውል ከመፈረም በፊት

  • ሁልጊዜ ኮንትራቱን ማንበብ - የሽያጭ አስተናጋጁ በሚናገርዎት ብቻ አለመተማመን። የሞባይ ስልክ ኮንትራት ውል በህግ የተጠበቀ ነው። ኮንትራቱን ለመሰረዝ ብዙጊዜ አስቸጋሪና ውድ ነው።
  • የተደበቀ ክፍያ ወጪና ተገቢ ያልሆነ የኮንትራት ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ቀድሞ ማወቅ ያስፈልጋል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት የእኛን ሞባይል ስልክ አቅራቢዎች - ተገቢ ያልሆነ የኮንትራት ቅድመ ሁኔታዎች የሚለውን ገጽ ማየት።
  • ላልተረዳዎት ኮንትራት በምንም መልኩ አለመፈረም - ኮንትራቱ ለተረዳው የሆነ ሰው ስለ ኮንትራቱ ማብራሪያ እንዲሰጥዎት መጠየቅ።
  • የወርሃዊ ክፍያ ምን ያህል እንደሆነ ማጣራት፣ እንዲሁም ማንኛውም ተጨማሪ ክፍያዎችን ማጣራት። ኮንትራቱ በሚቆይበት ጊዜ እነዚህን ክፍያዎች ማካሄድ ስለመቻልዎ እርግጠኛ መሆን።
  • የሞባይ እቃና የማስቀጠያን ከቸርቻሪው ላይ ከገዙት ሁለት የተለያዩ ኮንትራቶች ሊገቡ ይችላሉ - አንድ ለሞባይል እቃ ከቸርቻሪው ጋር ሌላው ደግም ለኔትዎርክ ማስቀጠያ ከአገልግሎት አቅራቢው ጋር ይሆናል። ይህ ማለት ከሞባይል ስልኩ ጋር በተዛመደ ችግር ካለ ቸርቻሪው ሊረዳዎት ሲችል ነገር ግን በማንኛውም የኔትዎርክ ግንኙነት ችግሮች ላይ አይረዳዎትም።
  • እድሜው ከ 18 በታች ለሆነ ሰው በኮንትራት ላይ 'ዋስትና ከማካሄድ' በፊት በጥንቃቄ ማሰብ - መክፈል ካልቻሉ የነሱን ፍጆታ ክፍያ ስለሚከፍሉ ነው።
  • ስለ መብቶችዎና እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በበለጠ ለመማር በእኛ የኮንትራት ገጽ ላይ ማየት።

ለሞባይል ስልክ ኮንትራት ውል ከፈረሙ በኋላ

  • ይኮንትራት ቅጂ ወረቀቱን በደህና ቦታ ማስቀመጥ ታዲያ አስፈላጊ ከሆነ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ማየት ይችላሉ።
  • የርስዎ ሁኔታ ከተቀየረ ለአገልግሎት አቅራቢዎ ማሳወቅ - ለምሳሌ፡ የሞባይል ስልክዎ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ፣ ወይም ለፍጆቻ ዋጋ ጥያቄ ለመክፈል አቅምዎ ካልፈቀደ።

ለሞባይል ስልክዎ የፍጆታ ዋጋ ጥያቄ ስለመቆጣጠር

  • በተደጋጋሚ ስለተጠቀሙት ጥሬ መረጃ አጠቃቀም መቆጣጠር - ይህ ለብዙ የፍጆታ ዋጋ ጥያቄ እንዳይቀርብ ሊረዳ ይችላል።
  • የርስዎ ፍጆታ ዋጋ ጥያቄ ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ እንዳለብዎና ስለ ማንኛውም ያልተለመደ ክፍያ ለአገልግሎት አቅራቢዎ ይጠይቃሉ።
  • ስለርስዎ ቀሪ ክፍያዎች ለማስላት ወይም ባጀት ለማውጣት እርዳታ ከፈለጉ ለ National Debt Helpline ማነጋገር።
  • የፍጆታ ዋጋ ጥያቄን በጊዜው ይክፈሉ። ካልከፈሉት፤ ለዘግይቶ ክፍያ ተጨማሪ ዋጋ ሊከፍሉ ይችላሉ።

ነገሮች በትክክል ካልተካሄዱ

  • ሞባይል ስልክዎን የገዙበትን ሱቅ፣ ወይም ለአገልግሎት አቅራቢዎ ማነጋገር። ምክሮች ለማግኘት የእኛን ቅሬታ ስለመፍታት የሚለውን ገጽ ማየት።
  • ከርስዎ የፍጆታ ዋጋ መጠየቂያ ጋር በተዛመደ ችግር ካለብዎት ወይም ከአገልግሎት አቅራቢዎት ጋር መፍታት የማይችሉት የኔትዎርክ ግንኙነት ችግር ካለብዎት ለ Telecommunications Industry Ombudsman ማነጋገር።